ነሀሴ 15 2017
በአዲስ አበባ በመጪው ዓመት ቢያንስ 500,000 ነባር የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች በዘመናዊ ቆጣሪዎች ይቀየራሉ ተባለ።
ነባሮቹ ቆጣሪዎች በሂደት ሙሉ ለሙሉ በዘመናዊ ቆጣሪዎች እንደሚተኩም ተነግሯል።
እስከ አሁን በሙከራ ደረጃ የቆየው አዲሱ ቆጣሪ ደንበኞች ካሉበት ሆነው የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን የሚያውቁበት እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
ዘመናዊዎቹ ቆጣሪዎች ደንበኞች ወደ ተቋማት መሄድ ሳያስፈልጋቸው በስልካቸው ካርድ እየሞሉየሚጠቀሙበትን ሥርዓትም የያዙ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የኤሌክትሪክ ኔትወርክ ቁጥጥር ሀላፊ አቶ ዘሪሁን አበበ ተናግረዋል።
Comments