የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ለምን በሚፈለገው ልክ አልሆኑም?
TRACK

የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ለምን በሚፈለገው ልክ አልሆኑም?

Avatar

ነሀሴ 14 2017

መንግስት በፓርቲ ጉባኤዎች ማጠቃለያ መግለጫም ሆነ በተለያዩ መድረኮች በሀገር ሰላም እንዲወርድ ለታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ቢያቀርብም በሚፈለገው ደረጃ ጥሪው ሰላም ማውረድ አልቻለም፡፡

የ2017 የህዝብ እንደራሴዎችን ምክር ቤት የስራ ዘመን አስመልክተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በበጀት ዓመቱ ብቸኛው ኃይል የመጠቀም መብት ያለው መንግስት ብቻ መሆኑን ጠቅሰው ሰላም በአገሪቱ ለማስፈን መስራት የመንግስት ዋና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው መንግስት ለሰላማዊ ንግግር እና ችግሮችን በንግግር ለመፍታትም ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመው ነበር፡፡

በርግጥ በየመሃሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች በተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ በአገር ሽማግሌዎች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ቀርበዋል፡፡

Comments

Avatar