በትውልድ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሣው በአሜሪካ ለአውሮራ ከተማ ም/ቤት አባልነት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡
TRACK

በትውልድ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሣው በአሜሪካ ለአውሮራ ከተማ ም/ቤት አባልነት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

Avatar

ነሀሴ 2 2017

በትውልድ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሣው በአሜሪካ ለአውሮራ ከተማ ም/ቤት አባልነት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

አቶ አምሳሉ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የማሟያ ምርጫ አሸንፈው በአሁኑ ሰዓት የከተማውን ሶስተኛ ከፍተኛ የአስተዳደር ቦታ ይዘዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተጓዙ 18 ዓመት እንደሆናቸው የነገሩን አቶ አምሳሉ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች በከተማው አገልግለዋል።

ባለፈው ዓመት በአውሮራ ከተማ ለምክር ቤት አባልነት በተካሄደ የማሟያ ምርጫ ከ37 እጩዎች ጋር ተፎካክረው ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን አሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪ በያዘችው የአውሮራ ከተማ የምክር ቤት አባል ሆነው ይሰራሉ።

በአሜሪካ የአሪዞና ግዛት ከ40,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩ የሚነገር ሲሆን የሚበዙትም መኖሪያቸው አቶ አምሳሉ የምክር ቤት አባል በሆኑበት የአውሮራ ከነማ እንደሆነ ይነገራል።

Comments

Avatar