ሰኔ 12 2017
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፍወርቅ ተክሌን የስነ ጥበብ ስራዎች እና ሌሎች ንብረቶች ከተረከበ በኋላ ያስቀመጣቸው ለአቧራ ተጋላጭ በሆነ ቦታ መሆኑ ተነገር ፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በበኩሉ የኪነ ጥበብ ስራዎችን የሚያነፍስ ራሱን የቻለ ለቅርስ ጥበቃ ባለሙያ ቀጥሪያለሁ ይላል፡፡
ይህ የተነገረው የመንግስት ወጭ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በባለስልጣኑ የተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምዝገባ ጥበቃ እና እንክብካቤን የስራ አፈጻጸም በተመለከት የ2015/16 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መነሻ በማድረግ የተቋሙ የስራ ሀላፊዎች ላይ ምላሽ እንዲሰጡባቸው ጥያቄ ከቋሚ ኮሚቴው ቀርቦባቸዋል፡፡
ቅርሶች በአግባቡ ጥበቃ፣ ምዝገባ፣ ጥገና እና እንክብካቤን እየተደረገላቸው መሆኑን መከታተሉን በተመለከተ በተደረገ ኦዲት ሲደረግ ባለይዞታዎች እና ባለቤቶች ቅርሶችን እንዲሁም በራሱ ይዞታ ስር ያሉ ስብስቦች በአግባቡ እንክብካቤና ጥገና እያደረጉ ስለመሆኑ ለመከታተል የሚያስችል አሰራር ሳይዘረጋ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡
Comments