በኢትዮጵያ የደም ህክምና የሚጠይቁ አንዳንድ የካንሰር ህመሞች ህክምና አለመኖር በታካሚዎች ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ
TRACK

በኢትዮጵያ የደም ህክምና የሚጠይቁ አንዳንድ የካንሰር ህመሞች ህክምና አለመኖር በታካሚዎች ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ

Avatar

ነሀሴ 20 2017

በኢትዮጵያ የደም ህክምና የሚጠይቁ አንዳንድ የካንሰር ህመሞች ህክምና አለመኖር በታካሚዎች ላይ ከሚያደርሰው ተጽዕኖ በተጨማሪ ሀገሪቱንም በህክምናው ቱሪዝም ዘርፍ ብዙ የውጪ ምንዛሪ የሚያሳጣ ሆኖ ዘልቋል ተባለ፡፡

የደም ህክምና የሚጠይቁ የካሰር ህመሞች እንደ አጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላና ሌሎች ተመሳሳይ ህክምናዎች በሀገር ቤት ለመስጠትም ስራዎች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ተናግሯል፡፡

ህክምናዎቹ ሀገር ቤት ባለመኖራቸው ብዙዎች እንደሚቸገሩ እንዲሁም ህይወታቸውንም እንደሚያጡ የሚናገሩት የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ታዬ በመጪው ዓመት ህክምናውን በሀገር ቤት ለመጀመሪያ የተጀመሩ ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡

Comments

Avatar