ያለፉትን 6 ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ስራ እስካሁን ያስገኘው ለውጥ እንዴት ያለ ነው?
TRACK

ያለፉትን 6 ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ስራ እስካሁን ያስገኘው ለውጥ እንዴት ያለ ነው?

Avatar

ሐምሌ 3 2017

ኢትዮጵያ የተራቆተ መሬቷን ለማከምና የአየር ንብረቱን በማስተካከል አለምን እየፈተነ ያለውና ለብዙ ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ በብርቱ እየሰራች እንደሆነ ይነገራል፡፡

ያለፉትን 6 ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞች በመትከል ከዚህ ቀደም በብዙ ተጎድተው የነበሩ መሬቶች እንዲያገግሙና በአካባቢ ጥበቃ ስራውም ላይ ለውጥ እንዲያመጡ ተደርጓል፡፡

ስራው በብዙ መልኩ የሚጠቅም እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ኢትዮጵያ የምትፈተንበትን እንደ ድርቅ የመሬት መንሸራተትና ለግብርና ምርት አስፈላጊ የሆኑ መሬቶች አሲዳማነት ለመቀነስ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ሀገር በቀል የሆኑ እዕዋት በአካባቢ ጥበቃ ላይ አስተዋጽኦ ከመስጠት ባለፈ ለመድኃኒት እና ለምግብነት የሚውሉት ላይ ምን ያህል ተሰርቷል እስካሁን የነበረው ስራ ያስገኘው ለውጥስ እንዴት ያለ ነው ስንል ጠይቀናል፡፡

Comments

Avatar