''ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውበጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል'' የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩ
TRACK

''ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውበጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል'' የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩ

Avatar

ነሀሴ 15 2017

ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ሰነዶችን በወጉ ሰንዶ የመያዝ ችግር እና የመሳሰሉት በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል ሲል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩ ተናገረ፡፡

በጦርነት የወደሙ ተቋማት መረጃዎች አለመገኘትም ሌላው ችግር ሆኖ ተነሷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ጥያሩ ፖሊሲዎችን በሚመለከት ኢንስቲትዩቱ በርካታ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ጥናትና ምርምሮች ያለበቂ መረጃዎችና ሰነዶች የማይከወኑ በመሆናቸው ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ከተቋማት ለማግኘት ስንሄድ ለመስጠት ፈቃደኛ አይሆኑም ብለዋል።

Comments

Avatar