ባለፈው ሰኞ ቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ  ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል
TRACK

ባለፈው ሰኞ ቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል

Avatar

ነሀሴ 2 2017

በቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከቀናት በፊት ከባድ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ።

ጉዳት ከደረሰባቸው እርሻዎች የተወሰኑት ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስ ረዘም ያለ ጊዜ እና ከፍተኛ ገንዘብ ሊጠይቃቸው ይችላል ተብሏል።

ባለፈው ሰኞ ቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

ዝናቡ በማምረቻ ሼዶች ፤ በአበባ ምርቶች እና በላብላቶሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱን ሠምተናል።

ሬንቦ ከለርስ የአበባ እርሻ ብቻ ስምንት ሄክታር ላይ የነበረ ምርት ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ እንደሆነበት ነግሮናል።

Comments

Avatar