TRACK
ማዕከላዊ ባንኩ በቂ የውጪ ምንዛሪ እና መደላድል አለ ቢልም ባንኮች ግን በምትኩ የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት እስከ 200% ተቀማጭ እየጠየቁ ነው ተብሏል
ሐምሌ 22 2017
የውጭ ምንዛሪ በገበያው እንዲወሰን ያስቻለ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ከተደረገ ዓመት ሆነው፡፡
ሪፎርሙ የብሔራዊ ባንክ የመጠባበቂያ ክምችትን ማሳደጉ፣ በወጪ ንግድ በመሳሰሉት ከፍተኛ ውጤት እንዲመጣ ማስቻሉ ተነግሯል፡፡
ለንግድ፣ ለትምህርት፣ ለጉብኝት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱ ሰዎችም ማሻሻያው ከተደረገ በኋላ በተሻለ መጠን ዶላር እየቀረበላቸው መሆኑም ይሰማል፡፡፡
ግን ባንኮች ዶላር ለጠየቃቸው እስከ 200 በመቶ ተቀማጭ እየጠየቁ ነው የሚል ክስ ቀርቧል፡፡
ማዕከላዊ ባንኩ በቂ የውጪ ምንዛሪ እና መደላድል አለ ቢልም ባንኮች ግን በምትኩ የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት እስከ 200% ተቀማጭ እየጠየቁ ነው ፤ ቢውሮክራሲም እያበዙ ነው ተብሏል።
Comments