በተለምዶው (ሿሿ) ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች
TRACK

በተለምዶው (ሿሿ) ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች

Avatar

ጳጉሜ 3 2017

በአዲስ አበባ በተለያዩ ጊዜያት ከማታለል ጋር የተያያዙ በተለይም በትራንስፖርት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ወይም በተለምዶው (ሿሿ) ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸው ይነገራል፤ ድርጊቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የሚሰማ መሆኑ የማታለል ወንጀሉን የሚፈጸሙ ግለሰቦችም የሚጠቀሙት መንገድ ተመሳሳይ መሆኑ ቢነገርም ወንጀሉ ተደጋግሞ መሰማቱ ከጥንቃቄ ጉድለት ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

ስለ ጉዳዩ የጠየቅነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በበኩሉ በየጊዜው ስለ ወንጀል ድርጊቶቹ አፈፃፀም ዝርዝር መረጃ እየሰጠን ግለሰቦችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ቢነገርም የሚተገበሩት ግን ጥቂቶች ናቸው ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደነገሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ በየጊዜው በሚደርሰው ጥቆማ እንዲሁም በሚያደርገው ድንገተኛ ፍተሻ ተጠርጣሪዎቹን እንደሚያገኝና ክስ እየመሰረተ ለፍርድ ቤት እያቀረበ ነው ብለዋል፡፡

Comments

Avatar