''ወጣቶች በግብርናው ዘርፍ መሰማራት የማይፈልጉት ዘርፉ በቴክኖሎጂ ባለመታገዙ እንደሆነ በሰራሁት ጥናት ደርሼበታለሁ'' ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ
TRACK

''ወጣቶች በግብርናው ዘርፍ መሰማራት የማይፈልጉት ዘርፉ በቴክኖሎጂ ባለመታገዙ እንደሆነ በሰራሁት ጥናት ደርሼበታለሁ'' ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ

Avatar

ሰኔ 19 2017

ወጣቶች በግብርናው ዘርፍ መሰማራት የማይፈልጉት ዘርፉ በቴክኖሎጂ ባለመታገዙ እንደሆነ በሰራሁት ጥናት ደርሼበታለሁ ሲል ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተናገረ፡፡

ይህን የሰማነው ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለ4ተኛ ጊዜ ያደረገው አዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ 2025 የስራ ፈጠራ ውድድር መዝጊያ ላይ ነው፡፡

የግብርናው ዘርፍን በሚያሳድጉ የስራ ፈጠራና ቴክኖሎጂዎች ላይ ብቻ የሚያተኩረው አዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ የፈጠራ ውድድር በዚህ ዓመት ከ319 የፈጠራ ሃሳቦች ውስጥ 5ቱ ውድድሩን ያሸነፉት ተወዳዳሪዎች 28,000 ዶላር ተሸልመዋል፡፡

የሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስየሺወርቅ አየለ ተቋማቸው በዋናነት ትኩረት ያደረገው በኢትዮጵያ ርሃብን ማጥፋትና ግብርናው በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ማድረግ ነው፡፡

ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ ወጣቱ በዚህ ዘርፍ እንዲሳተፍ ማድረግ ይገባል ነገር ግን ወጣቱ ወደ ግብርና እየገባ አይደለም የአዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ ውድድር አላማ አድርጎ የተነሳው ቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡

ከዚህ ቀደም በተደረጉ ውድድሮች ያሸነፉ የስራ ፈጣሪዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንከታተላለን የሚሉት አቶ ቴዎድሮስየሺወርቅ ሄፈር በተሰማራባቸው ዘርፎች የሚወጡ የፈጠራ ሃሳቦች ከባለሙያዎቹ ጋር በመሆን ወደ ስራ እናስገባለን ብለዋል፡፡

Comments

Avatar