ነሀሴ 16 2017
ከመስከረም እስከ ታህሳስ ያሉ ወራት የወባ በሽታ በስፋት የሚከሰትባቸው እንደሆኑ ይነገራል።
ህብረተሰቡም ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
በዚሁ ዙሪያ የሚሰራ አንድ ሀገር በቀል ድርጅት በበኩሉ የበሽታው ስርጭት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሆኖ የቀጠለበት አንዱ ምክንያት ስለ ህመሙ ያለ የተሳሳተ አረዳድ በመሆኑ እሱም ላይ መስራት ይገባል ብሏል።
በኢትዮጵያ አጠቃላይ የወባ ስርጭት በስፋት የሚከሰተው ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉ ወራት እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የዘንድሮውን የክረምት ዝናብና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ጎርፍ ተከትሎም ከመስከረም ወር አንስቶ በሽታው ሊከሰት ይችላል በሚል የጥንቃቄ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
በየቦታው የተጠራቀመው የክረምቱ ዝናብ በቀጣይ ከሚኖረው ከፍተኛ ሙቀት ጋር ተዳምሮ ለበሽታው መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ሊፈጠር ይችላል በሚል ነው መልዕክቱ እየተላለፈ የሚገኘው፡፡
Comments
awesome. keep it up. have a great weekend. God bless us. Amen/Allah. greetings from south africa