ሐምሌ 16 2017
ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር ያገናኛል የተባለው በቱርኩ ያፒ መርከዚ ተቋራጭ ከ10 ዓመት በፊት 1.7 ቢሊየን ዶላር የተመደበለት የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ጉዳቱ ተጠንቶ ተለይቷል ተባለ።
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈፅሞበታል የተባለው ፤ ስራውም ተቋርጦ የቆየው ይህ ፕሮጀክት እንደገና ለመቀጠልም ስራ መጀመሩ ተሰምቷል።
ባቡሩ ከጦርነት እና ግጭት ባለፈ በተፈጥሮ ፤ መሬት መንቀጥቀጥ ጭምር የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ጉዳት እንደደረሰበት ተረድተናል።
የዚህን ፕሮጀክት ዳግም ጀምሮ ለማጠናቀቅ ጉዳቱ እንደተለየና በእቅድ እንደተያዘ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው ነግረውናል።
Comments