ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ 17ኛው ባለብዙ ዘርፍ አውደ ጥናት አካሄደ
TRACK

ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ 17ኛው ባለብዙ ዘርፍ አውደ ጥናት አካሄደ

00:00

ሐምሌ 11 2017

ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ 17ኛው ባለብዙ ዘርፍ አውደ ጥናት አካሄደ።

ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ በሚያካሄደው የባለብዙ ዘርፍ አውደ ጥናት ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ የምርምር ስራዎች በሚገባ ተሰንደው ለፖሊሲ አውጪዎችና ለሌሎችም ለሚመለከታቸው አካላት እየሰጠሁ ነው ተብሏል፡፡

ባለፉት 17 ዓመታት ይህ ጉባኤ ሲካሄድ ነበር በዚህ አውደ ጥናት ላይ የቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች በተገቢው መንገድ ከተመረመሩ በኋላ ተሰንደው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሳቸው ተደርጓልም ተብሏል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ወንድወሰን ታምራት(ዶ/ር) በዚህ ጉባኤ የሚቀርቡ ጥናቶች ዋነኛ መስፈርታቸው ሀገሪቱ በወቅቱ ከያዘቻቸው እቅዶች ጋር የሚሄዱ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የምርምር ስራዎቹ ሲመረጡም ተግባራዊነት ያላቸውና የሚያመጡት ለውጥና ተፅዕኖ ትኩረት ይደረግባቸዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።

Comments

00:00