የቤንሻንጉል ጉሙዝን ከኦሮሚያ እና አማራ በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ተጨማሪ ሰዎች የታጠቁ ሃይሎችን ጥቃት በመስጋት እየተፈናቀሉ ነው ተባለ፡፡
TRACK

የቤንሻንጉል ጉሙዝን ከኦሮሚያ እና አማራ በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ተጨማሪ ሰዎች የታጠቁ ሃይሎችን ጥቃት በመስጋት እየተፈናቀሉ ነው ተባለ፡፡

Avatar

ሐምሌ 3 2017

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ተጨማሪ ሰዎች የታጠቁ ሃይሎችን ጥቃት በመስጋት ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ነው ተባለ፡፡

በዚህ አይነቱ ስጋት በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከ40,000 ወደ 45,000 ከፍ ማለቱን ሸገር ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሠምቷል።

ከኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጋር አዋሳኝ በሆኑ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ተጨማሪ ሰዎች፤ በታጣቂዎች ሊፈጸም ይችላል ያሉትን ጥቃት በመስጋት ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።

በቅርቡም ክልሉን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስነው የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ የሶስት ቀበሌ ነዋሪዎች እንደተፈናቀሉ፤ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።

ከካማሺ ዞንም እንዲሁ ከ5,000 በላይ ሰዎች በዚሁ ስጋት በቅርቡ ተፈናቅለዋል ብለዋል።

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሃይሎች ደግሞ ከ1,300 በላይ የክልሉ ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ኮሚሽነር መሃመድ ነግረውናል።

ተፈናቃዮቹ ዳንጉር እና ማንዱራ በተባሉ ቦታዎች ነዋሪ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

Comments

Avatar