የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አባል የሆኑበት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር፤ በመጪው ዓመት ዓመታዊ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ያካሄዳል ተባለ
TRACK

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አባል የሆኑበት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር፤ በመጪው ዓመት ዓመታዊ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ያካሄዳል ተባለ

Avatar

ሐምሌ 28 2017

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አባል የሆኑበት የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር በመጭው ዓመት ዓመታዊ ኮንፈረንሱን በኢትዮጵያ ያካሄዳል ተባለ፡፡

ኮንፈረንሱ የሚካሄደው የአፍሪካ ቢዝነስ ስኩል ማህበር ከክቡር ኮሌጅ ጋር በጋራ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በዚህም በ2018 ዓ.ም የሚያሰናዳውን ዓመታዊ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች የተባለ ሲሆን ዝግጅቱ በመጪው ዓመት ከግንቦት 12 እስከ 14 ቀን በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ይህን የሰማነው የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማህበር ከክቡር ኮሌጅ ጋር በመሆን በተሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ከ150 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዳይሬክተሮች እና የአለም አቀፍ አካዳሚክ መሪዎች ከመላው አፍሪካ እና ከዓለም አቀፍ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Comments

Avatar