ነሀሴ 16 2017
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ ( #ኦፌኮ) በ2018 ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ አስቻይ ሁኔታ ከሌለ ላይሳተፍ እንደሚችሉ ተናገረ፡፡
ፓርቲው ይህን ካደረገ ለሁለት ተከታታይ ምርጫ ራሱን ያገልላል ማለት ነው፡፡
የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ከወራት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ ላይ ለመሳታፍ ተንቀሳቅሶ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እና በነጻነት ለመምረጥ አስቻይ ሁኔታ ያስፈልጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ፓርቲው ከ4 ዓመት በፊት ተደርጎ በነበረው ሀገራዊ ምርጫም አልተሳተፈም፡፡
በቀጣይ በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የማይሳተፍ ከሆነ ደግሞ በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ መሰረት ህጋዊ እውቅናው ይሰረዛል፡፡
Comments