የዓለም የምግብ ፕሮግራም በእ.ኤ.አ 2024 መጨረሻ ላይ ይዞት በወጣው ሪፖርቱ 15.8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የዕለት ጉርስ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል
TRACK

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በእ.ኤ.አ 2024 መጨረሻ ላይ ይዞት በወጣው ሪፖርቱ 15.8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የዕለት ጉርስ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል

Avatar

ሐምሌ 17 2017

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በእ.ኤ.አ 2024 መጨረሻ ላይ ይዞት በወጣው ሪፖርቱ 15.8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የዕለት ጉርስ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የምግብና ግብርና ተቋም እንደሚለው ከሆነ ደግሞ አሁን ባለንበት 2025 ብቻ ኢትዮጵያ 3.6 ሚሊየን አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የዕለት ጉርስ ለሟሟላት 128 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በመረጃው መሰረት ኢትዮጵያ የግብርና ስርዓቷንና የአመጋገብ ወጓን ካላዘመነች የምግብ ዋስትና ስጋቷ እየተባባሰ ይሄዳል፡፡

የግብርና ምርምርና ጥናት ባለሞያው ፀደቀ አባተ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የምግብ ሰብል አማራጮቿን ማስፋት አለባት ይላሉ፡፡

‘’መሬት ላራሹ ሲታወጅ አንድ የአርሶ አደር ቤተሰብ በነፍስ ወከፍ 10 ሄክታር የእርሻ መሬት ነበረው’’ ያሉት ባለሞያው ‘’አሁን የአንድ ቤተሰብ የእርሻ መሬት ይዞታ ወደ 0.81 ሄክታር ዝቅ ብሏል’’ ብለዋል፡፡

Comments

Avatar