ሐምሌ 22 2017
አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ( #IMF ) በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ላይ ስጋት አለኝ ብሏል፡፡
የፀጥታ ችግሮች እልባት አለማግኘታቸው፣ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ዋጋ መካከል ልዩነቱ እየሰፋ መሄዱ፣ የታሰበውን ያህል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አለመገኘቱ፣ እርዳታና ድጋፎች መቀነሳቸውና ሌላውንም በማንሳት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ወደ ኋላ ሊያንሸራትተው ይችላል ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከIMF ጋር ለ4 ዓመት ውል አስራ እየተገበረችው ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተቋሙ ከሳምንት በፊት ያወጣው ሪፖርት ለሶስተኛ ጊዜ ግምገማ ካደረገ በኋላ ይፋ ያደረገው ነው፡፡
በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ወደ ኋላ ሊወስዱ ይችላሉ ያላቸውን ስጋቶችን በዝርዝር አሳውቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፕራግማ ካፒታል ስራ አስፈፃሚ እና የኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ በተቋሙ የተነሱት ስጋቶች ትክክል መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
Comments