00:00
ነሀሴ 8 2017
በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት ፍሳሽ ቆሻሻ በማፋሳሻ ቦዮች እንዳያስወግዱ መከልከሉ በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
መኖሪያ ቤታቸው የተጠጋጉና በቂ ቦታ በሌላቸው ቤቶች የፍሳሽ ቆሻሻ ጉድጓድ ቆፍሩ መባላችን ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡
የከተማዋ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ በፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ማለፍ የሚችለው የዝናብ ጎርፍ ብቻ ነው ብሏል፡፡
ነዋሪዎች በግቢ ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረን ፍሳሹን ብናጠራቅምም ለማስመጠጥ ተቸግረናል ሲሉ ነግረውናል፡፡
የትኛውንም ፍሳሽ ቆሻሻን ማስወገድ የሚቻለው በጊቢ ውስጥ በተቆፈረ ጉድጓድ ብቻ እንደሆነ የተናገረው ባለስልጣኑ የተጠራቀመውን ውሃ ማስመጠጥ አልቻልኩም የሚል ነዋሪ ካለ ከሚመለከታቸው ጋር ለማገናኘት ዝግጁ ነን ብሏል፡፡
መሰረተ ልማት ሳይሟላ ክፈሉ የምንባለው ቅጣት ከአቅማቸው በላይ ነው ሲሉም ነዋሪዎቹ አማርረዋል፡፡
Comments
00:00