መምህራን በእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያመጡት ውጤት ደካማ ሆኖ መመዝገቡን ተነገረ
TRACK

መምህራን በእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያመጡት ውጤት ደካማ ሆኖ መመዝገቡን ተነገረ

Avatar

ሐምሌ 21 2017

ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው የ2ኛ ደረጃ የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠና የተሳተፉ መምህራን በእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያመጡት ውጤት ደካማ ሆኖ መመዝገቡን ተነገረ፡፡

ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ መምህራን ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የአቅም ማሻሻያ ስልጠና በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

43,000 የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ገብተው ከወሰዱ በኋላ ፈተና ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ፈተናውን ከወሰዱ መምህራን መካከል 61.4 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 የክረምት የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠናን በተመለከተ አጠቃላይ ትንተና መስራቱን ተናግሯል፡፡

Comments

Avatar