ዶ/ር አብዱ አደም የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል
TRACK

ዶ/ር አብዱ አደም የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል

Avatar

ሐምሌ 21 2017

ኢትዮጵያዊው ከፍተኛ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም፤ የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው መሾማቸው ተነገረ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የካንሰር ህክምና ክፍል ከፍተኛ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር አብዱ አደም የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል።

በዚህም ዶ/ር አብዱ ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የካንሰር ክብካቤ እና ህክምና (ኦንኮሎጂ) ባለሙያዎችን ይደግፋሉ ተብሏል።

የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) በካንሰር መከላከል ላይ የሚከውናቸውን ስራዎች እንዲሁም በካውንስሉ ውስጥ ስለተሰጣቸው ኃላፊነት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር አብዱ አደም ጠይቀናል፡፡

Comments

Avatar