TRACK
የሚያጋጥሙ የተፈጥሮም ይሁን የሰው ሰራሽ አደጋዎችን ተከትሎ ክልሎች እራሳቸውን ችለው ተረጅዎችን እንዲረዱ በመንግስት ትዕዛዝ ከተሰጣቸው ሰንበትበት ብሏል
00:00
ነሀሴ 21 2017
የሚያጋጥሙ የተፈጥሮም ይሁን የሰው ሰራሽ አደጋዎችን ተከትሎ ክልሎች እራሳቸውን ችለው ተረጅዎችን እንዲረዱ በመንግስት ትዕዛዝ ከተሰጣቸው ሰንበትበት ብሏል፡፡
ይህም ሆኖ የሚደርሰው አደጋ ከክልሎች አቅም በላይ ከሆነ መንግስት ድጋፍ አያቀርብም ማለት እንዳልሆነም ተነግሯል፡፡
ይሁን እንጂ በድርቅ ፣በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ችግር ምክንያትና የተፈናቀሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን የያዙ ክልሎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡
በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ብቻ ከፍተኛ የተፈናቃይ ቁጥር ካለባቸው አካባቢዎች መካከል የደቡብ ኢትዮጵያና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች ይገኙበታል፡፡
ሁለቱ ክልሎች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በመሬት ናዳ ምክንያት ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉባቸው ናቸው፡፡
Comments
00:00