በትምህርት ቤት ዙሪያ አዋኪ ድርጊት ሲፈፅሙ የተገኙ 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ ተባለ፡፡
TRACK

በትምህርት ቤት ዙሪያ አዋኪ ድርጊት ሲፈፅሙ የተገኙ 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ ተባለ፡፡

Avatar

ሐምሌ 4 2017

በትምህርት ቤት ዙሪያ አዋኪ ድርጊት ሲፈፅሙ የተገኙ 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ ተባለ፡፡

በትምህርት ቤት ዙሪያ በ500 ሜትር ራዲየስ አዋኪ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ነበሩ ያልኳቸውን 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተፈቀደላቸው ቦታ ውጪ የበረንዳ ንግድ በሚነግዱ 7,394 ደንብ ተላላፊዎች ላይም እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ ይህንን ያለው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎቹን በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

ሌላኛው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚቆጣጠራቸው ህገ-ወጥ ተግባራት አንዱ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻን በሚመለከት መሆኑ የተነገረ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ 12,140 ማስተካከያ ባለደረጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን መቅጣቱን ተናግሯል፡፡

Comments

Avatar