ነሀሴ 1 2017
በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ያመጡት አሉታዊና አዎንታዊ ለውጥ በጥናት መፈተሽ አለበት ተባለ፡፡
ይህን ያሉን ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሞያ ናቸው፡፡
ባለፉት ተከታታይ 3 ዓመታት የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ዝቅ ማለቱን ተከትሎ በተማሪዎች የመማር ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያመጣ ስጋት አለን የሚሉ ባለሞያዎች በተለያዩ ጊዜያት እየተደመጡ ነው፡፡
እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት አብዛኛው ተማሪ ውጤት እየመጣለት ባለመሆኑ በትምህርት ዘርፍ ላይ ተስፋ እንዳይቆርጥ ስጋት አለን በማለት ሲናገሩ ይሰማል፡፡
የትምህርት ባለሞያና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዳምጠው ወልዴ(ዶ/ር) አሁን ያለው ተማሪ ከፈተና ውጤት ጀምሮ በየጊዜው የሚያያቸው ቴክኖሎጂዎች በትምህርት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገው ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ጥናት አልተደረገም ችግሩ ከስር መሰረቱ በሚገባ ለማወቅና ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ለመስጠት ጥናትና ምርምር ሊደረግ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
Comments